የቤተክርስቲያነችን የዜማ መሳሪያዎች እንደ ዜማው ሁሉ  ፍጽም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉም አላቸው


  1. ለምሳሌ ከበሮ




    • ይህ የዜማ መሣሪያ በቁሙ የጌታችንን የመድሐኒታች የእየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው።ከበሮ ሁለት ገጽዎች ያሉት ሲሆን አንደኛው ገጽ ሰፋ ያለ ሁለተኛው ገጽ ደግሞ ጠበብ ያለ የዜማ መሣሪያ ነው።ሰፊው ገጽ የመለኮት ምሳሌ ነው ይሀውም መለኮት (ሙልዕ በኩልየ)በሁሉ ቦታ ያለ መሆኑን ለማዘከር ነው።ጠበቡ ገጽ ደግሞ የአምላክን በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት መወሰኑን ለማጠየቅ ሲሆን ሁለቱ ግጻት ተደራጅተው አንድ ከበሮ አንደሆኑ የመለኮትና የስጋ ውሀደት ፍጽም መሆኑን ያጠይቅልናል።የከበሮ አካል የተሸፈነበት ጨርቅ አንድም አይሁድ ለመዘባበቻ ያለበሱትን ከለሜዳ መታሰቢያ ነው በጨርቁ ላይ ከላይ ወደታች የተጠላለፈው ጠፍርጌታችንመድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በአይሁድ በተገረፈ ግዜ በሰውነቱ ላይ የወጣውን ሰንበር ለማዘከር ነው።