ሰኔ 12 (፲፪)
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
"+ እንኩዋን ለሊቀ መላእክት # ቅዱስ_ሚካኤል እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ
በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+
=>በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት ‪#‎ቅዱስ_ሚካኤልን‬ ጨምሮ ‪#‎ቅዱስ_ላሊበላ‬
: # ቅድስት_አፎምያና # ቅዱስ_ባሕራን_ቀሲስ ይከበራሉ::
+"+ ‪#‎ቅዱስ_ሚካኤል‬ ሊቀ መላእክት "+
=>ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ ‪#‎በኢዮር‬ : ‪#‎ኃይላት‬ በተባሉት ነገደ
መላእክት ተሹሞ ነበር:: ሳጥናኤል በካደ ጊዜ እግዚአብሔር ባወቀ: አንድም
በትሕትናውና ደግነቱ በ99ኙ ነገደ መላእክት ላይ ሁሉ ተሹሟል::
+ከፍጥረት ወገን ‪#‎ከእመቤታችን‬ ቀጥሎ የቅዱስ ሚካኤልን ያሕል ክብርና
ርሕሩሕ የለም:: በምልጃውም: በረዳትነቱም የታወቀ መልአክ ነው::
መጽሐፍ "መልአከ ምክሩ ለእግዚአብሔር" ይለዋል:: "ወስሙ
መስተሣሕልም" ይለዋል:: ቂም የሌለው: ለምሕረት የሚፋጠን: ደግ
መልአክ ነውና::
+በብሉይ ኪዳን በመከራ ለነበሩ ቅዱሳን ሁሉ ሞገስ: ረዳትና አዳኝ
ቢሆናቸው "መጋቤ ብሉይ" ተሰኝቷል:: እሥራኤልን 40 ዘመን በበርሃ
መርቷል: መግቧልም:: ቅዱስ መጽሐፍ ስለ እርሱ ብዙ ይላል:: (ዘፍ.
48:16, ኢያ. 5:13, መሳ. 13:17, ዳን. 10:21, 12:1, መዝ. 33:7,
ራዕይ. 12:7)
+ደስ የሚለው ደግሞ ርሕሩሑ መልአክ ከእመቤታችን ጋር ልዩ ፍቅር
አለው:: ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ እስከ ዛሬ እነሆ አብሯት አለ:: ደስ ብሎት
ይታዘዛታል:: ማማለድ ሲፈልግም "እመቤቴ ሆይ! ቅደሚ" ይላታል:: ወደ
እሳት መጋረጃ አብረው ገብተው ለዓለም ምሕረትን: በረከትን ያወርዳሉ::
+ቅዱስ ሚካኤልን በዚሕች ዕለት ስለ እነዚህ ነገሮች እናከብረዋለን:-
1.በመላእክት ሁሉ ላይ አለቃ ሆኖ መሾሙን
2.ቅዳሴ ቤቱን (ግብፅ ውስጥ)
3.ቅድስት አፎምያን መርዳቱን
4.ቅዱስ ባሕራንን መጎብኘቱን
5.ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ማሳረጉን
6.ለፍጥረታት ሁሉ ምሕረት የሚጠይቅበት ዕለት ነውና::
=>ሊቀ መላእክት በክንፈ ረድኤቱ ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን::
+"+ # ቅዱስ_ላል_ይበላ ንጉሥ "+
=>በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ ላይ በሃገራችን የነገሠው ቅዱስ
ላሊበላ:-
¤በብሥራተ መልአክ ተወልዷል
¤ቅዱሳት መጻሕፍትን ገና በልጅነቱ አጥንቷል
¤የንጉሥ ዘር ቢሆንም በጾምና ጸሎት: በትሕርምት አድጉዋል
¤በወንድሙ ቢገረፍም ቂም አልነበረውም
¤ስለ ወዳጆቹ ፍቅር መርዝ ጠጥቷል
¤በዙፋን ላይ የኢትዮዽያ ንጉሥ ሆኖ ቢቀመጥም እርሱስ አኗኗሩ ገዳማዊ
ነበር
¤ከተባረከች ሚስቱ ቅድስት መስቀል ክብራ ጋር አንዲት ማዕድ ብቻ በቀን
ይቀምሱ ነበር:: ለዛውም ለምለሙን ለነዳያን ሰጥተው እነርሱ የሚበሉት
የእንጀራውን ቅርፍት (ጠርዝ) ብቻ ነበር::
+በአካለ ሥጋ ወደ ሰማያት ተነጥቆ ብዙ ምሥጢራትን አይቷል
¤በምሳሌውም ሃገረ ሮሃን (ላስታን) ገንብቷል
¤ዛሬም ድረስ ምስጢር የሆኑት ፍልፍል አብያተ መቃድስ የእጆቹ ሥራዎች
ናቸው::
+ሥራውን ከፈጸመ በሁዋላ መንግሥቱን ለቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አውርሶ:
በመንኖ ጥሪትና በቅድስና ኑሮ በዚሕች ቀን አርፏል:: ጌታችን ስምህን
ያከበረ: ዝክርህን የዘከረ: ከቤትህ ያደረውን: ከርስተ መንግስተ ሰማያት
አካፍለዋለሁ ሲል ቃል ኪዳን ገብቶለታል::
=>በረከቱን: ክብሩን ያድለን::
+"+ # ቅድስት_አፎምያ +"+
=>ከቅዱስ አስተራኒቆስ ጋር በተቀደሰ ትዳር የኖረ
¤ምጽዋትን ያዘወተረች
¤በፍቅረ ቅዱሳን የጸናች
¤ንጽሕናዋን ጠብቃ ሰይጣንን ያሳፈረች ደግ እናት ናት:: ዛሬ የቅዱስ
ሚካኤልን ስዕል ታቅፋ: በትእምርተ መስቀልም አማትባ አርፋለች: ቅዱሱ
መልአክም ወደ ገነት አሳርጉዋታል::
+"+ # ቅዱስ_ባሕራን ቀሲስ +"+
=>የደጋግ ክርስቲያኖች ግን የድሆች ልጅ:
¤በሕጻንነቱ በግፍ ወደ ባሕር የተጣለ:
¤በእግዚአብሔር ጥበብ አድጎ የግፈኛውን ንብረት የወረሰ:
¤በመልካም ትዳር በቅስና ያገለገለ:
¤ምጽዋትን ያዘወተረ: አብያተ ክርስቲያናትን ያሳነጸ ደግ ክርስቲያን ነው::
¤በዚህች ቀን አርፎ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጁ በዕረፍተ ገነት አኑሮታል:
=>አምላካችን እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ በረከት ይክፈለን:: አሜን::
ወስብሃተ ለእግዚአብሔር ወወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ፍቁር ለአለም ዘላለሙ አሜን