ጾምና ጥቅሙ | ![]() | ![]() |
መጋቢት 8ቀን 2008 ዓ.ም.
ከሊቀ ጉባዔ ቀለመወርቅ ውብነህ
ጾም ለተወሰነ ሰዓት ከሁሉም ምግብ መከልከል፣ ሁሉንም ምግብ መተው ሲሆን ለተወሰነ ቀናት ማለት የጾሙ ቀናት እስኪያልፍ ድረስ ከተወሰኑ ምግቦች መከልከል የተወሰኑ ምግቦችን መተው ነው፡፡ ይህም ጥሉላትን ፈጽሞ መተው፣ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጾም ከጥሉላት ምግቦች መከልከል ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጆችን ከሚጎዳ ነገር ሁሉ መከልከልና ለሌሎች መልካም ሥራ መሥራትንም ይጨምራል፡፡
ጾም ከሃይማኖት ጋር ዘለዓለማዊ የሆነ ዝምድና እና ጥብቅ ቁርኝት አለው፡፡ ጾም የራሱ የሆነ ሕግጋትና ሥርዓት ስለአለው ጾም ለምን እንደሚጾም፣ ለማን እንደሚጾም፣ መቼ እንደሚጾም፣ እንዴት እንደሚገባና እንዴት እንደሚወጣ ለይቶ የሚያሳውቅ የራሱ የሆነ ሕግና ደንብ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ጾም በብሉይ ኪዳን ከፍተኛ ቦታ የነበረው ሲሆን፣ የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ጋር በሚገናኙበት /ጊዜ/ ወራት እህልና ውኃ በአፋቸው አይገባም ነበር፡፡ /ዘፀ.34፥28/ በሰው ልጆች በደልና ኃጢአት ብዛት የታዘዘው የእግዚአብሔር መቅሠፍት /መዓት/ የሚመለሰው /የሚወገደው/ ሕዝቡ በጾምና በጸሎት ሲለምኑትና ሊማልዱት እንደነበር /ዮናስ.2፥7-10/ ተጠቅሶ ይገኛል፡፡እንደÃàቅዱስ ጴጥሮስና እንደ ቆርኔሌዎስ ማለት ነው፡፡ /የሐ.ሥራ 10፥3-9Ãàለተወሰነ ሰዓትም ከቆዩ በኋላ ጿሚው የሚበላው ዳንኤል በጾመ ጊዜ እንዳደረገው ከቅባት ነጻ የሆነ ምግብ ነው፡፡ âበዚያን ወራት አኔ ዳንኤል ሦስት ሣምንት ሙሉ ሳዝን ነበርኩ፡፡ ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም፡፡ ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም፡፡ ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም ይላል፡፡ /ዳን.10፥2-3/ ጾም ለነፍስ ብቻ ሳይሆን ለሥጋም መድኀኒት እንደሆነ ጥቂት ነጥቦችን እናነሳለን፡-
የጾምንና የጸሎትን ኃይል ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ሲያስረዳ እንደዚህ ዓይነቱ ርኩስ መንፈስ በጾምና በጸሎት አማካይነት ካልሆነ በስተቀር አይወጣም ብሏቸዋል፡፡ /ማቴ.17፥21/ጾም የራስን በደል አምኖ፣ ጸድቶ፣ ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ በድያለሁ ማረኝ በማለት የእግዚአብሔርን ይቅርታ ለማግኘት የሚረዳ ታላቅ መሣሪያ ነው ሳሙ.7፥5-6፡፡የጾም ጥቅሙና አገልግሎቱ በጥንቱ ዘመን ከአበው ጀምሮ በግልጽ የታወቀ እንደ ነበረ ቅዱሳት መጻሕፍት በሚገባ ያስረዳሉ፡፡ በሙሴ ዘመን ጾም የተገለጸው የተቀደሰ ጉባዔ ወይም ራስን ማስጨነቅ በሚል አነጋገር ነው /ዘሌ.16፥19፣ 23፥27፣ ዘኁ.29፥7Â ጾም የሚጾመው ከእግዚአብሔር ሊያገኙት የሚገባ ጸጋንና በረከትን፣ ይቅርታንና ምኅረትን፣ ለማግኘት ነው፡፡ ሙሴ በደብረ ሲና 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾሞ በግብር አምላካዊ የተጻፉ ዐሥርቱ ቃላትን ተቀብሏል /ዘፀ.34፥28፣ ዘዳ.9፥9-15/፡፡
ጾም ጸሎትና ስግደት፣ ጾም ከእግዚአብሔር ጋር በቀጥታ የሚነጋገሩበት ቋንቋ የሚገናኙበት ድልድይ ወይም መሰላል በመሆኑ በንጽሕናና በቅድስና የሚፈጸም ሥርዓት ነው /ነህ.9፥1-3/፡፡ÃÃÂ ጾም ከተንኮልና ከክፋት ከመሰላሰሉት የሰይጣን ሥራዎች ሁሉ ርቆ ስለ ራስና ስለ ሕዝብ ሥርየት ኃጢአትን ሰላምና በረከትን ለመለመን፣ ፊትን ወደ እግዚአብሔር ማቅናት ነው፡፡ /ዳን.9፥1-19፣ 6፥18/የጾምና የጸሎት ውጤትም በንጹሕ ልቡና እና በቀና ኅሊና ለሚጾመው ሰው በመላእክት አማካይነት ይገለጻል /ዳን.9፥20/፡፡ጾም ወደ እግዜአብሔር አቤቱታ የማቅረብያ መንገድ በመሆኑ ያልታሰበ ችግርና ፈተና ሲያጋጥም፣ ሕዝብ እንዲጾም፣ እንዲጸልይ፣ በእግዚአብሔር ፊት ራሱን እንዲያዋርድ አዋጅ ይነገራል፡፡ /ዕዝ.8፥21፣ አስ.4፥3፣ ኤር.37፥9፣ ኢዮ.1፥13-14/ ይመለከቷል፡፡ የዐቢይ ጾም ሁለተኛው ሳምንት እሑድ ቅድስት ይባላል፡፡
ይህም ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና የሚያወሳ ነው፡፡ ቅዱስ እግዚብሔር የረከሰውን ዓለም ለመቀደስ በመጣ ጊዜ ከጥምቀቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈጸመው ተግባር ለሰው ልጅ ቅድስና ሲል፣ እንደ ሰው ገዳም ገብቶ መጾም፣ መስገድ፣ በጸሎት መትጋት ነበር፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠምቆ ዕለቱን ገዳመ ቆሮንቶስ ወደሚባል ምድረ በዳ ሄዶ በዚያ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾሟል፡፡ ማቲ.4፥1-2፡፡ 40ውን ቀን ጾመ ቢባልም እህል ውኃ ሳይቀምስ ነው እንጂ እንደኛ ጾም ውሎ ማታ እየተመገበ ሲደክም ውሎ ሌሊት አርፎ እያደረ አይደለም፡፡ /ሉቃ.4፥2/ ሳይበላና ሳይጠጣ 40 ቀንና 40 ሌሊት ሙሊ በመጾም ክብረ ጾምን አስተምሮናል፡፡
ቅድስት
ቅድስት ማለት የተቀደሰች፣ የተባረከች፣ ንጽሕት ማለት ነው፡፡ ጾምን ቀድሱ ጉባኤውን አውጁ ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፡፡ ኢዮ.1፥14 በኢዩኤል አፍ የተናገረ ቅዱስ እግዚአብሔር የጾማት ጾም ስለሆነች ቅድስት ትባላለች፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዲያብሎስን ፈተና ድል ለመንሳት በቅድስት ከተማ በሰሎሞን ቤተ መቅደስ ጫፍ የቆመባት ዕለት በመሆኗ ቅድስት ትባላለች ማቴ. 4፥5፣ ዮሐ.10፥22-23፡፡ ቅድስት የቤተ ክርስቲያን ማዕከል የመቅደስና የቅኔ ማኅሌት ሁለተኛው ክፍል የምእመናን መጸለያ፣ የካህናት ሥጋ ወደሙ ማቅረቢያ፣ መቅረዝና የዕጣን መሠዊያ; የተቀደሰች የእግዚአብሔር ማደሪያ ናት ዘፀ.23፥33-35፣ 30፥6፣ ዕብ.9፥2፡፡
ቅድስተ ቅዱሳን፣ ከቅዱሳን ይልቅ የተቀደሰች፣ ከከበሩ የከበረች መቅደስ ኦሪት ቅድስት 20 ክንድ ቅዱሳን የሚባሉት መቅደስና ቅኔ ማኅሌት 40ው ክንድ ናቸው፡፡ ቅድስት፣ ዕለተ ሰንበት እግዚአብሔር ሰባተኛይቱን ቀን ባረካት፣ ቀደሳት ዘፍ.2፥3፣ ዘፀ.20፥8፡፡ ቅዱስ ያሬድም ሰንበትየ ቅድስትየ እንተ አዕረፍኩ እምኲሉ ግብርየ ይቤ እግዚአብሔር ብሏል፡፡ ቅድስት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ መዝ.95፥5 በእነዚህና በመሳሰሉት ሁለተኛዋ ሳምንት ቅድስት ትባላለች፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ |