| ዘመነ ጽጌ |
መስከረም 24 ቀን 2005 ዓ.ም.
በመ/ር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ
ክረምቱ አልፎ በጋ ሲተካ ተራውንም ለዘመነ መፀው ሲያስረክብ የመጀመሪያው ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6 ያለው ወቅት ዘመነ ጽጌ
ማኅሌተ ጽጌ የተባለው የድርሰት ክፍል እመቤታችንን በጽጌ ማለት በአበባ ልጇን መድኀኔዓለምን በፍሬ እንደገናም እሷንም ልጇንም በአበባና በፍሬ እየመሰለ ልብን በሚመስጥ ምሥጢራት ስለ እመቤታችን ድንግል ማርያምና ስለ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚናገር ድርሰት ሲሆን፤ በውስጡ ስለ ሥላሴ፣ ስለ ቅዱሳን መላእክት፣ ስለ ቅዱሳን ነቢያት፣ ስለ ቅዱሳን ሐዋርያት፣ ስለ ቅዱሳን ሰማዕታትና ስለ ቅዱሳን ጻድቃን የሚናገርና ገድላቸውን ትሩፋታቸውን መከራቸውን ከብሉይ ከሐዲስ አስማምቶ የሚገልጽ መጽሐፍ ነው፡፡
ነገረ ማርያምን ስደቷን፣ መራቧን፣ መጠማቷን፣ ማደሪያ አጥታ በምድረ በዳ መንከራተቷን፣ መቸገሯን፣ በድንግልና ከወለደችው ውድ ልጇ ጋራ የደረሰባትን ጭንቅና መከራ በሚያሳዝንና ልብን በሚሰብር ጣዕም የሚያስረዳ ነው፡፡ ይህም ከመሆኑ የተነሣ ሊቃውንትም ሆኑ ምእመናን ዘመነ ጽጌ እስከሚመጣ ይጓጓሉ፣ ይናፍቃሉ፣ ዘመነ ጽጌ መጥቶ እስኪያልፍ ድረስ ከሌሎች ሰንበታት በተለየ መልኩ ማታ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ መላ ሌሊቱን የእመቤታችንን ስደቷን በማሰብ፡-
|