ከኣርያም ይሰማል ውዳሴው

ከኣርያም ይሰማል ውዳሴው
በምስጋና ይሞላል ማደሪያው
በኣንድነት ሶስትነት የሰለሳል
አንደ ስላሴ ያለ ማን ይሆናል
         በዘባነ ኪሩብ ተቀምጧል በፊቱ
         የማይፈራው የለም አሱን የማያከብር
         ለመንግስቱ ሽረት ፍጻሜ የሌለው
         ሁሉን የሚያሳልፍ ዘላለማዊ ነው
ከኣርያም ይሰማል ውዳሴው
በምስጋና ይሞላል ማደሪያው
በኣንድነት ሶስትነት የሰለሳል
አንደ ስላሴ ያለ ማን ይሆናል
ሰውን ኣበጃጀው ከኣፈረ አንስቶ
አስትንፋስ ሂዎተን ለዘላለም ሰቶ
ከህሊና በላይ ነው ኣነዋወሩ
አንዳተከበረ ይኖራል በክብሩ