ገሊላ ግቢ»
እመቤቴ እስከመቼ ባዕድ አገር ትኖሪያለሽ ፣
ገሊላ ግቢ ገሊላ ግቢ፣
አገርሽን ገሊላ ግቢ፣
ገሊላ እትዊ።
እመቤቴ ማርያም ስደቱ ይበቃሻል፣
ሔሮድስ ሙቷል ብሎ ገብርኤል ነግሮሻል፣
በእሳት ሰረገላ ዑራኤል ይመራሻል።
የዝናቡ ጌታ እናት ሁነሽ ሳለ፣
ሰይጣን በሰው አድሮ እያስከለከለ፣
ውኃ ጥም ፀንቶብሽ አፍሽ ደርቆ ዋለ።
ይበቃል እናቴ ረሀብ ጥማትሽ፣
ሂጅ ወደ ገሊላ ወደ ዘመዶችሽ።
ሀገርኪ ገሊላ እትዊ፣
ሀገርሽ ገሊላ ግቢ።