*** ገሊላ እትዊ***
"ተፈጸመ ናሁ ማኀሌተ ጽጌ ስሙር
እስምኪ ቦቱ ንግስተ ሰማይ ወምድር"
ወደ ሃገርሽ ጊቢ ድንግል ወላዲቱ
የመከራው ጊዜ አብቅቶል ስደቱ
የዓለሙን ቤዛ ልጅሽን ታቅፈሽ፣
ያን የግብፅ በረሃ አሸዋን አቋርጠሽ፣
ትንሽ ብላቴና አንድ ፍሬ ሳለሽ፣
ያ ጨካኙ ንጉስ ሄሮድስ አሳደደሽ።
ከደረቅ አለት ላይ ውሃ የሚያፈልቅ ልጅሽ
አቅፈሽው ይዘሽው ሁሉን የሚሰጥሽ
ትንቢቱ እንዲፈፀም ጥምን ግን ተጠማሽ
ስምኦን እንዳለው ሰይፍ ያልፋል በነፍስሽ
በስደት ጀመረ መከራ ስቃይሽ።
አንቺ ደጓ እመቤት ያየሽው መከራ
ፀሐይ ሀሩር ሳትይ ከአንድ ልጅሽ ጋራ
አንባን እየዘራሽ ከሰሎሜ ጋራ
በረሃን ያቋረጥሽ ከዮሴፍ ጋራ
ንጉስ ሞቷልና አንቺን ያሳደደሽ
ሂጂ ወደ ገሊላ አብቅቷል ስደትሽ
ሶላማጢስ ድንግል ጊቢ ወደ ሀገርሽ
ያንቺ ምልጃ ይርዳን የእናትነት ፍቅርሽ
በስደት ላለነው ለአስራት ልጆችሽ!!!
***አሜን***( በምስጢረ ድግሴ)
እስምኪ ቦቱ ንግስተ ሰማይ ወምድር"
ወደ ሃገርሽ ጊቢ ድንግል ወላዲቱ
የመከራው ጊዜ አብቅቶል ስደቱ
የዓለሙን ቤዛ ልጅሽን ታቅፈሽ፣
ያን የግብፅ በረሃ አሸዋን አቋርጠሽ፣
ትንሽ ብላቴና አንድ ፍሬ ሳለሽ፣
ያ ጨካኙ ንጉስ ሄሮድስ አሳደደሽ።
ከደረቅ አለት ላይ ውሃ የሚያፈልቅ ልጅሽ
አቅፈሽው ይዘሽው ሁሉን የሚሰጥሽ
ትንቢቱ እንዲፈፀም ጥምን ግን ተጠማሽ
ስምኦን እንዳለው ሰይፍ ያልፋል በነፍስሽ
በስደት ጀመረ መከራ ስቃይሽ።
አንቺ ደጓ እመቤት ያየሽው መከራ
ፀሐይ ሀሩር ሳትይ ከአንድ ልጅሽ ጋራ
አንባን እየዘራሽ ከሰሎሜ ጋራ
በረሃን ያቋረጥሽ ከዮሴፍ ጋራ
ንጉስ ሞቷልና አንቺን ያሳደደሽ
ሂጂ ወደ ገሊላ አብቅቷል ስደትሽ
ሶላማጢስ ድንግል ጊቢ ወደ ሀገርሽ
ያንቺ ምልጃ ይርዳን የእናትነት ፍቅርሽ
በስደት ላለነው ለአስራት ልጆችሽ!!!
***አሜን***( በምስጢረ ድግሴ)