“ድንግል ማርያም ሆይ ፦ የኔ ምህረት በልጅሽ ዘንድ ስላንቺ አይደንቅም ፡ ስለ ስምሽም የኔ ይቅር መባል በልጅሽ ዘንድ አይደንቅም ፡ ስለ ፀሎትሽም የኔን ሐጢኣት ማቅለል በልጅሽ ዘንድ አይደንቅም፡፡ ስለ ልመናሽ የኔን እዳ በደል ማቅለል በልጅሽ ዘንድ አይደንቅም ፡ ባንቺ እታመናለሁ ፦ በዚህ አለም ከፀብ ከክርክር ከሞት ታድኝኝ ዘንድ በሚመጣውም አለም ማእበል ሞገድ ከሚፈላው የእሳት ባህር ታድኝኝ ዘንድ፡፡ ድንግል ሆይ ፦ እታመንሻለሁ ከተሰወረው መከራ በግልፅም ከሚመጣብኝ ጥፋት ሁሉ በዚህ አለም እንድታድኝኝ ፡ በሚመጣውም አለም ከገሃነመ እሳት ጥርስ ማፋጨት ፅኑ ልቅሶም ካለበት ከሚያስጨንቅ መቅሰፍት ትሰውሪኝ ዘንድ እኔም ባንቺ አማላጅነት በልጅሽም ምህረት የታመንሁ ነኝ፡፡ በፈረሰኞች ሰልፍ በሰረገላም መንኮራኩር የምታመን አይደለሁም ፡ ባንቺና በልጅሽ ብቻ እታመናሉህ እንጂ፡፡ “ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አርጋኖን ዘ እሑድ —